25ኛው የዓለም ወጣቶች ቀን በክፍለ ከተሞች በድምቀት ተከበረ።
25ኛው የዓለም ወጣቶች ቀን በክፍለ ከተሞች በድምቀት ተከበረ።
ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የተደመረ የወጣቶች አቅም ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት" በሚል መሪ ቃል፣ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በድምቀት ተከበረ
በዓለም ለ25ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች በፓናል ውይይት እና በልዩ ልዩ ዝግጅት ማክበራቸውን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ንቅናቄ ቡድን አሳውቀዋል
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ በሰላም ግንባታ የወጣቶች ሚና፣ የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣ በጎ ፈቃድና ወጣቶች፣ የበጎ ፈቃደኝነት ጥቅሞች በሚሉ ጭብጦች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
የዓለም ወጣቶችን ቀን ማክበር ዋና ዓላማ የዘላቂ ልማት ግቦች ዕቅድ ስኬትን ማጠናከር እና አጋርነትን ማጠናከር ነው ያሉት የወጣቶች ግንዛቤና ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጤናዬ ታምሩ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመቀልበስ ወጣቱ ሚናውን እንዲጫወት የማስቻል ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል
ከማዕከል እስከ ወረዳ በሚደረግ የፓናል ውይይት ከ47ሺ በላይ ወጣቶች እንዲሳተፉ የገለጹት አቶ ጤናዬ ከአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ ግንዛቤ እንደሚፈጠርላቸው አመልክተዋል
ከተማ አቀፍ የዓለም ወጣቶች ቀን በነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ በድምቀት እንደሚካሄድ ከዳይሮክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል
የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 

እናመሰግናለን


ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219


ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014


ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet


ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/


ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.