ከጊጋሊ የተገኘው ልምድ ወደ አዲስ አበባ ለማስፋ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከጊጋሊ የተገኘው ልምድ ወደ አዲስ አበባ ለማስፋፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

ከጊጋሊ የተገኘው ልምድ ወደ አዲስ አበባ ለማስፋፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ ነሐሴ 17 ቀን 2 017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ከሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ ያገኘውን ዘመናዊ የአሰለጣጠን ስልት ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ ከ20 በላይ የአፍሪካ አገራት በተሳተፋበት ውድድር ላይ 24 የአዲስ የልኡካን ቡድን አባላትን መሳተፋቸውን ያስታወሱት ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ በስፍራው በመገኘት ዓለም የቀሰሙት ልምድ እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ከኪጋሊ የተገኘው ምርጥ ተምክሮ ቢሮው በመቀመር በ90 ቀናት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር አካቶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ጎሳዬ በ28 የስልጠና ጣቢያዎች 993 ታዳጊ ወጣቶች ተከታታይ ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ከአሜሪካን ኤንባሲ እና ኢትዮ ቦለርስ ጋር የቅርጫት ኳስ ልዪ ስልጠና ማስጀመሩን ያስታወሱት የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነህ በስልጠና ጣቢያዎች ያሉ ተሞክሮዎችን ማስፋት በአገር አቀፍ የውድድር መድረኮች ከተማ አስተዳደሩን የሚወክሉ ምርጥ ቡድን ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.