5ተኛው የልደታ ክፍለ ከተማ የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ
5ተኛው የልደታ ክፍለ ከተማ የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ ነሐሴ 19 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሲካሄድ የቆየው 5ተኛው የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አገኘ ለተከታታይ ሁለት ወራት በሦስት የእድሜ ደረጃ በድምቀት ሲካሄድ ቆይቶ የተጠናቀቀው የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ታዳጊ ቡድኖች መሳተፋቸው ተመልክቷል፡፡ ክፍለ ከተማው ለሁለት ተከታታይ ወራት ያካሄደው የ5ተኛው የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር ውጤታማ መሆኑን ያስታወሱት የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ የእግር ኳስ ውድድሩ በሦስት የእድሜ ደረጃ መካሄዱን አስታውቀዋል፡፡ ውድድሩ የተሳታፊ ወጣቶችን የእግር ኳስ ክህሎት በማዳበር ረገድ መልካም አጋጣሚ እንደነበረ ያወሱት አቶ ክብርዓለም ጨዋታው የቡድን መንፈስ በመገንባት የመማማርና የእርስ በእርስ ትስስርን ያጠናከረ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ወጣቶች በአንድ መድረክ በማገናኘት ማህበራዊ ትብብር የሚያጠናክሩ ውድድሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያረጋገጡት አቶ ክብርዓለም ውድድሩ አዲስ ተወዳዳሪዎችን ከማፍራት ባሻገር ትልቅ የውድድር ልምድ ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የውድድሩ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች ከከተማ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ ለወዳደር ራሳቸውን ያሳዩበት ነው ያሉት አቶ ክብርዓለም በበጋው መርሃ ግብር እንደዚህ አይነት ውድድሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com
+4
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች49Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 47 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.