አቶ በላይ ደጀን ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማሕበር አመራሮች ጋር በማህበሩ ሁለንተናዊ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
አቶ በላይ ደጀን ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማሕበር አመራሮች ጋር በማህበሩ ሁለንተናዊ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
ነሐሴ 21 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር አመራሮች ጋር በማህበሩ ሁለንተናዊ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
ቢሮው የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እንዲጠናከርና ለከተማዋ ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚሰራ ጠንካራ ማህበር እንዲሆን የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ በላይ ተናግረዋል።
ማህበሩ በጠቅላላ ጉባኤው የአመራር ለውጥ ካካሄደ በሆላ አደረጃጀቱን ከወረዳ እስከ ከተማ በማጠናከር እየሰራው ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ግልፅ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንዳለበት አቶ በላይ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ፕሬዘዳንት ወጣት በረከት ቢርቢሳ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣትችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እንዲጠናከር በየጊዜው የሚያካሂደውን ድጋፍና ክትትል አድንቀው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የመዲናዋ ወጣቶች በከተማዋ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲያካሂዱና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮና ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማህበሩ እየሰራ እንደሚገኝ ወጣት በረከት ተናግረዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 

እናመሰግናለን


ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219


ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014


ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet


ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/


ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/


ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.