የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፌስቲቫል በየካ ክፍለ ከተማ ተካሄደ
የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፌስቲቫል በየካ ክፍለ ከተማ ተካሄደ
ነሐሴ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የየካ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት በለውጡ የተለወጠ ወጣት በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፌስቲቫል በድምቀት አካሄደ
በፌስቲቫሉ ላይ ከሁሉም ወረዳ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ አማተር የኪን ጥበብ ቡድኖች፣ባህላዊ እና ዘመናዊ ዳንስ ክበባት፣ በማዕከላት የሚሰሩ ልዩ ልዩ ስፓርት ሰልጣኞች የስፓርት ትርኢት፣የድምጽ ባለተስጥኦዎች ስራ፣የሞዴሊንግ ትርኢት፣የስዕል አውደ ርዕይ እና አጫጭር ተውኔቶች ለዕይታ ቀርበዋል
በፌስቲቫሉ ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ብስራት ማጆሬ የነገ አገር ተረካቢ ወጣቶችን በአዕምሮ ለማነጽ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ ገልጸዋል
የአገር ሁለንተናዊ ዕድገት ባላት ሃብት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ዜጋ ማፍራት ሲቻል ነው ያሉት አቶ ብስራት ሙስናን የሚጸየፍ የአገር ፍቅር ያለው ወጣት ለማፍራት በየደረጃው የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል
የፌስቲቫሉ ዋና ዓላማ ወጣቶች ያላቸዉን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም ህብረ_ብሄራዊ ወንድማማችነትና አህትማማችነትን ማጠናከር መሆኑን የቀድሞ የወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሱባለው መንደዶ
ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የበገራችንን ባህልና ወግ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ እሱባለው የወጣቶች ጉዳይ በሁሉም አካል ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመልክተዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 

እናመሰግናለን


ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219


ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014


ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet


ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/


ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/


ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.