የቦሌ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ፌስቲቫል በድምቀት ተካሄደ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
የቦሌ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ፌስቲቫል በድምቀት ተካሄደ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት በለውጡ የተለወጠ ወጣት በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፌስቲቫል በድምቀት አካሄደ በ24 ሜዳ በተካሄደው ፌስቲቫል ላይ የሁሉም ወረዳ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የሰልፍ ትርኢት፣ አማተር የኪን ጥበብ ቡድኖች ባህላዊ እና ዘመናዊ ዳንስ ክበባት ውድድር፣በማዕከላት የሚሰሩ ልዩ ልዩ ስፓርት ሰልጣኞች ትርኢት ለዕይታ ቀርበዋል የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከለውጥ ወዲህ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ያስታወሱት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚሰሩ ወጣቶች የሚያካሂዱት ፌስቲቫል ችሎታን ከማሳደጉ በላይ አብሮነትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል ወጣቶች የኢትዮጵያን ብልጽግና ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ግንባር ቀደም ተዋንያን መሆናቸውን ያወሱት ዶ/ር እሸቱ ለማ አገራዊ ለውጡ በወጣቶች ተሳትፎና መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አሰፋ በበኩላቸው ፌስቲቫሉ ሀገራችን በማንሰራራት ምዕራፍ ላይ በምትገኝበትና ታላላቅ የለውጥ ትሩፋቶች እያስመዘገበች ባለችበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል ብለዋል፡፡ ወጣቱን በሥነ ምግባር ለማነጽ በአካሉ እና በአዕምሮ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ማዕከላት ሚናቸውን እየተወጡ ነው ያሉት አቶ አንዷለም ወጣቶች ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ ከማሳለፍ በመቆጠብ ፍሬያማ ልምዳቸውን ከተጠቃሚዎች እንዲወስዱ አሳስበዋል ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.