ቢሮው የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራን ጨምሮ በ90 ቀናት ታቅደው የተፈፀሙ ተግባራት ላይ ውይይት አካሄደ።
ቢሮው የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራን ጨምሮ በ90 ቀናት ታቅደው የተፈፀሙ ተግባራት ላይ ውይይት አካሄደ። ጳጉሜ 03 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራን ጨምሮ በ90 ቀናት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከከተማው ወጣቶች ክንፍ እና ወጣት ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ቢሮው የከተማው ወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በ90 ቀናት ታቅደው በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደሆኑ ተናግረዋል። ቢሮው ለስራ እድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ያሳወቁት አቶ በላይ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ስራ ፈላጊ ወጣቶችን ምዝገባን ጨምሮ እየተሰጡ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥሉ እንደሚገባ አቶ በላይ አሳስበዋል። የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎ ሌላው ቢሮው በ90 ቀናት ትኩረት አድርጎ እየሰራው የሚገኝ ተግባር መሆኑን የተናገሩት የቢሮው ሀላፊው በቀጣይ ቀናትም ወጣቶችን በማህበራዊ እና በስብዓዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ማሳተፈ እንደሚገባ አሳስበዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም የስራ እድል ፈጠራን ጨምሮ በቀጣይ ቀናት የ90 ቀናት ለመፈፀም የታቀዱ ተግባራትን ለማጠናቀቅ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.