ቢሮው ከጆርካ ኢቨንት ጋር በመተባበር የበዓል ስ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ቢሮው ከጆርካ ኢቨንት ጋር በመተባበር የበዓል ስጦታ አበረከተ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ቢሮው ከጆርካ ኢቨንት ጋር በመተባበር የበዓል ስጦታ አበረከተ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ከጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ኃላፊነቱ ከተወሰነ የግል ማሕበር ጋርጋር በተባበር ለሃገር ባለውለታ ለሆኑ አንጋፋ አትሌቶች፣ ስፓርተኞች እና አቅም ደካሞች የአዲስ ዓመት መዋያ የበግ ስጦታ አበረከተ ዛሬ በአፍሪካ ሕብረት ገበያ ማዕከል በተካሄደው የበዓል ስጦታ መርሃ ግብር ላይየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ መክብብ ወልደሃና የጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ለአንጋፋ አትሌቶች፣ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ አቅመ ደካሞች እና ለበጎ አድራጎት ማህበራት የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሃምሳ በላይ የበግ ስጦታ ተበርክቷል ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን በመቋቋም ድልን የተቀናጀችበት ታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በመረቁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት አቶ በላይ ግድቡ የጀመርነውን እንደምንፈጽም ማሳያ ከመሆኑም ባሻገር የተፋሰሱ ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል እንዲህ አይነት በጎ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ስራዎች ባህል ሆነው መቀጠላቸውን ያወሱት አቶ በላይ የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ያስጠሩ እና አቅመ ድካሞችን የማገዝ ስራ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል ጠንካራ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማንነት በአብሮነታችን እንደሚደምቅ ዛሬ ያደረግነው የበዓል ስጦታ ማሳያ ነው ያሉት አቶ በላይ ከቢሮው ጋር በቅንጅት እየሰራ ለሚገኘው ጆርካ ኢቨንት ምስጋና አቅርበዋል የሀገራችን ኢትዮጵያ ባለውለታ የሆኑ አቅመ ደካሞችን በዘላቂነት ለመደገፍ ሁሉም ሃገር ወዳድ በጋራ መስራት አለበት ያሉት ቢሮ ኃላፊው በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን በመልካም ምኞታቸው ገልጸዋል ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.