የክረምት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የክረምት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር የመዝጊያ ዝግጅት ተካሄደ ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ/ም

የክረምት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር የመዝጊያ ዝግጅት ተካሄደ ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ23 የስፖርት አይነት በክረምት በታዳጊ ወጣቶች ስልጠና መርሃ ግብር ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ታዳጊዎችን አስመረቀ የነገው ቀን ምክንያት በማድረግ በቤል ኤር ሜዳ በተካሄደው የምርቃት መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የአራ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሁኔ መሐመድ፣ ራዕይ ቤል ኤር የታዳጊዎችና ወጣቶች የእግር ኳስ ፕሮጅፕክት ሰልጣኞ፣ ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል በአመስቱ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በ23 የስፓርት አይነት ከ60ሺ በላይ ታዳጊዎች መሰልጠናቸውን ያስታወሱት አቶ ዳዊት ትርፉ ከታችኛው የእድሜ እርከን ጀምሮ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል ታዳጊ ወጣቶች ላይ በስፋት መስራት ለነገ የስፓርት ትንሳኤ መረጋገጥ ዋስትና ነው ያሉት አቶ ዳዊት ታዳጊዎችን ወደ ክለብ ወደሀገር አቀፍ ስፖርት አካዳሚዎች እና ለብሄራዊ ቡድን ለማሸጋገር የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሁኔ መሀመድ በበኩላቸው የከተማችን ስፓርት በሁለም የስፓርት መስክ ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ተስፋ የተጣለባቸው ታዳጊ ስፓርተኞች ራሳቸውን ለማብቃት በበጋና ክረምት በሚሰጠው ስልጠና እንዲሳተፉ ጠይቀዋል የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.