በአዲስ አመት ለከተማችን ነዋሪዎች እነሆ ገፀ በ...

image description
- ውስጥ supporter    0

በአዲስ አመት ለከተማችን ነዋሪዎች እነሆ ገፀ በረከት “አዲስ-መሶብ”! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አመት ለከተማችን ነዋሪዎች እነሆ ገፀ በረከት “አዲስ-መሶብ”! የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራታችንን ቀጥለናል:: ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት "አዲስ መሶብ "የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ አስጀምረን በአዲሱ አመት ዋዜማ እነሆ ገፀ በረከት ብለናል። በአስራ ሶስት ተቋማት ፤ መቶ ሰባት አገልግሎቶችን የሚሰጠው አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የነዋዎቻችን እንግልት የሚቀንስ ፣ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አዲስ ብስራት ይዘን መጥተናል። በአዲሱ አመት በብዙ ብርታት እና ትጋት ልናገለግላችሁ ቆመናል ። መልካም አዲስ አመት ! ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.