በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺህ በላ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።

በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ። መስከረም 02 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ተካሄደ። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ጨምሮ ከ300ሺ በላይ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የአባይ ግድብ ኢትዮጵያዊያን በህብረት አንድ ላይ ስንቆም የማናሳካው ፕሮጀክት የማንፈፅመው ገድል እንደሌለ ለዓለም ያሳየንበት ድንቅ ታሪክ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል። የሕዳሴ ግድብ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሀብታም እስከ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በጋራ ያሳኩት መሆኑን ያወሱት ምክትል ከንቲባው የህዳሴው ግድብ መጠናቁ ለሀገራችን ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ተጠቀሜታ ባሻገር በህብረተሰቡ ዘንድ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ያጠናክራል ብለዋል። የኢትዮጵያውያን የላብ ፣ የደም እና የእንባ መስዋዕትነት የከፈሉበት ስለመሆኑም ማስታወስ ያሻል ያሉት አቶ ጃንጥራር የአባይ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት የአዲስ አበባ ነዋሪ እና አመራሩ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ማማ ለመድረስ የሚያስችላት ቁልፍ መሳሪያ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን አዲስ አበባ ውስጥ እየተቀየረ የመጣው የወጣቶች መልካም ስራ ባህል ኢኮኖሚውን ከፍ እንዳደረገው ገልጸዋል። የአባይን ግድብ ማጠናቀቃችን ለሌላ ስኬት እና ድል የሚያነሳሳን ነው ያሉት አቶ በላይ ግድቡ አገር የሚጠቅም እንዲሆን መንግስትና ሕብረተሰቡ ያደረጉት የአርበኝነት ተጋድሎ ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል ብለዋል። ለአባይ ግድብ የወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት አቶ በላይ በቀጣይ በሀገራቸው ሁለንተናዊ ልማት እና ሰላም ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ የከተማ ነዎሪዎችም የአባይ ግድብ መጠናቀቁ ከፍተኛ ደስታና ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። እንዲህ በሌሊት ወጥተን ደስታችንን የምንገልፀው በሕዳሴ ግድብ የግንባታ ቦታ ሌት ተቀን ተግተው እቅዱን ላሳኩት ትጉህ እህት ወንድሞቻችን ያለንን አክብሮት ለማሳየት ነው" ሲሉ ተሳታፊዎች አክለዋል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.