የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ ዋና ዋና ጎደናዎች የስፖርት ፌስቲቫልና እና ትርዒት ተካሄደ።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ ዋና ዋና ጎደናዎች የስፖርት ፌስቲቫልና እና ትርዒት ተካሄደ።

መስከረም 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች የስፖርት ፌስቲቫል እና ትርኢት ተካሂዷል።

''በህብረት ችለናል'' በሚል መሪ ቃል መነሻውን ሽሮ ሜዳ በማድረግ የተካሄደውን የስፖርት ፌስቲቫልና የጎዳናላይ ትርዒት ያስጀመሩት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ የአባይ ግድብ የዚህ ትውልድ ደማቅ አሻራ እና ምልዕክት ነው ብለዋል።

የመዲናዋ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የአባይ ግድብ ከተጀመረበት ጀምሮ አበርክቶቸው ከፍተኛ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ በላይ ግድቡ መጠናቀቁ ከፍተኛ የደስታ ስሜት እንደፈጠረባቸው አሳውቀዋል።

የህዳሴው ግድብ መጠናቀቁ ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባሻገር ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣይ እንደሀገር ለማሳካት ላቀድናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን የቢሮ ሀላፊው ገልፀዋል።

28 ኪሎ ሜትር የሸፈነው የስፖርት ፌስቲቫልና የጎዳና ላይ ትርዒት መነሻውን ሽሮ ሜዳ በማድረግ በ6ኪሎ በአራት ኪሎ_ በአዳዋ ድል መታሰቢ _ በቸርቸል ጎዳና_ በለገሀር በመስቀል አደባባይ_ በቦሌ ደንበል _በቦሌ ኤርፖርት _ በመገናኛ በማድረግ ሰሚት በሚገኝው አፍሪካ ኮንቬሽን ሴንተር ፍፃሜውን አድርጎል።

በዚህ የስፖርት ፌስቲቫልና የጎዳናለይ ትርዒት ከ10ሺህ በላይ ብስክሌተኞች፣ ስኬተሮች፣ ፈረሰኞች እንዲሁም ሰርከከስ ትርዒት አቅራቢዎች፣ የማርሻሻል አርት ቤተሰቦች እና በከተማው የሚገኙ 36ቱም ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ተሳታፊ ሆነዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.