ከ10 አመት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከ10 አመት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም መድረክ ስመ ጥር ይሆናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) መስከረም 7 2018ዓ.ም

ከ10 አመት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም መድረክ ስመ ጥር ይሆናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

መስከረም 7 2018ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከ10 አመት በኋለ በአፍሪካና በዓለም የእግር ኳስ መድረኮች ስመ ጥር ብሔራዊ ቡድን ይኖራታል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጽፎ ለንባብ የበቃው 'የመደመር መንግሥት' መጽሐፍ የምረቃ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ብሔራዊ ቡድኑን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በሁለትና ሶስት አመት ውስጥ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት ከባድ ሊሆን ቢችልም፥ ከ10 አመት በኋላ በአፍሪካና በዓለም መድረክ ስመ ጥር ብሔራዊ ቡድን እውን ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ይህ በምኞት ሳይሆን በስራ የተገለጠ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለአብነትም በአዲስ አበባ ከተማ ከ100 በላይ መለስተኛ ስታዲየሞች መገንባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህ ስራዎች ለእግር ኳሱ እድገት ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ ይህን መስራት ሳይቻል የቴሌቪዥን መስኮት በማየት መቆጨት ብቻውን የሚለውጠው ነገር እንደማይኖር አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለነገ ውጤት የዛሬ ስራ መሰረት መሆኑን ጠቁመው፥ መንግሰትም ይህን ታሳቢ በማድረግ መሰረት የሚሆኑ ስራዎችን እየከወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

FBC

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.