የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን ወደ መዲናዋ ለማምጣት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን ወደ መዲናዋ ለማምጣት ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። አቶ በላይ ደጀን መስከረም 8 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን ወደ መዲናዋ ለማምጣት ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። አቶ በላይ ደጀን

መስከረም 8 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመዲናዋ ከሚገኙ የእግር ኳስ ለስፖርት ክለብ አመራሮች፣ ደጋፊዎች እና ለስፖርት ባለሙያዎች በስፖርዊ ጨዋነት ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ በአዲስ አበባ ከተማም እንዲካሄድ ከኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ስፖርታዊ ውድድሮች ካለምንም የፀጥታ ችግር በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄዱ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎችን ጨምሮ ሁሉም አካል ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት የተናገሩት አቶ በላይ ቢሮው በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የሚሰጠውን ስልጠና አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

የስፖርዊ ውድድሮች ስፖርታዊ መልዕክቶች ብቻ የሚተላለፋባቸው መድረኮች መሆናቸውን ያሳወቁት አቶ በላይ የተለያ አጀንዳ በመያዝ ወደ ሜዳ የሚገቡ እና የፀጥታ ችግር የሚፈጥሩ አካላትን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ ቴክኖሎጅን መሰረት ያደረግ አሰራር ለመከተል እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

አቶ ዳዊት ትርፋ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው በ2018ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን ጨምሮ ሀጉራዊ እና አለም አቀፍዊ ስፖርት ውድድሮችን አዲስ አበባ ከተማ እንዲካሄዱ በማድረግ የከተማዋን ብሎም የሀገርን መልካም ገፅታ ለመገንባት እንዲሁም አዲስ አበባን የቱሪስት መስህብ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ የስፖርት ሙሁር የሆኑት ዳ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል።

ለዘመናዊ እግር ኳስ ዘመናዊ ደጋፊን መፍጠር እንደሚያስፈልግ የገለፁት ዳ/ር ወገኔ በስልጠናቸው ደጋፊዎች ክለቦቻቸውን ለመደገፍ ወደ ሜዳ ሲመጡ ሊከተሎቸው የሚገቡ ስፖርታዊ ባህሪያት እና በቀጠይ ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን የስፖርት ክለቦት ሊሰሯቸው በሚገቡ ቅድመ ስራዎች ላይ ማብረራሪያ ሰጥተዋል።

በስልጠናው ላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ የቢሮው አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚዎች እና በኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ላይ የሚሳተፋ 6ቱ የአዲስ አበባ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.