ቢሮው በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄደ መስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም
ቢሮው በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄደ መስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ በመስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ዙሪያ ከመላው ሰራተኛ ጋር ውይይት አካሄደ የአደባባይ በዓላት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ አዱኛ መስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ ኅብረ ብሔራዊነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በዓላቱ የሰላም፣የፍቅር፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት መገለጫ ናቸው ያሉት ወይዘሮ መቅደስ በዓሉ ለማክበር ከአጎራባች ከተሞች የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ማስተናገድ እንደሚገባ አሳስበዋል በመስቀል እና ኢሬቻ በዓል አስመልክቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ገለጻ ያደረጉት አቶ ቃልአብ የዘንድሮ በዓል ታላላቅ ድሎችን በስኬት ባጠናቀቅንበት ማግስት በመሆናቸው አንድነታችን ለማጠናከር ትልቅ ትርጉም አላቸው ብለዋል ትውልዱ አንድነቱን በማጠናከር ያለፈውን ታሪክ በማክበር የራሱን ታሪክ እየሰራ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ ቃልአብ በይቅርታ መንፈስ በጋራ በእሴቶች ከሰራን የበለጸገች አገርን መገንባት ይቻላል ብለዋል መስከረም በገባ በየዓመቱ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት የመስማማት ፣የአንድነት፣የፍቅር እና የእርቅ ባህሎች ናቸው ያሉት አቶ ቃልአብ ማህበረሰቡ ከብረት በጠነከረ አንድነት ካለምንም ልዩነት ሲያከብረው መቆየቱን አስታውሰዋል የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ሰላምን፣ ፍቅርን፣አንድነትና የእኛነት እሴቶቻችን ምናጎለብትባቸው መሆናቸው ያወሱት አቶ ቃልአብ የአደባባይ በዓላቱ የኩራታችን ምንጭ፣የቱሪዝም እና የገቢ ምንጮች ሆነው እንዲቀጥሉ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.