የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ የመዲናችን ወጣቶችና ስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። አቶ በላይ ደጀን
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ የመዲናችን ወጣቶችና ስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። አቶ በላይ ደጀን
መስከረም 09 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ከ11ዱም ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማህበር እና ከአዲስ አበባ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ የመዲናችን ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባዋል ብለዋል።
ሁለቱም በዓላት በአለም በዩኒስኮ በማይዳሰሱ ቅርስነት የተመዘገቡ እና የኢትዮጵያን መለያ የሆኑ የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች በዓላቱን ለማክበር ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በመፈፀም ማክበር እንደሚገባ አቶ በላይ አሳውቀዋል።
የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት የፍቅር እና የሰላም መገለጫ የአንድነትና የመተባበር ማሳያ በዓላት በመሆናቸው በዓላቱ ሳይበረዙ እሴቶቻቸውን ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ወጣቱ እና የስፖርት ቤተሰቡ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አካላትም የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ኢሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በዓላቱን ለማክበር ከአጎራባች ከተሞች እና ከሌሎች አከባቢዎች ወደ መዲናችን የሚመጡ እንግዶችንም በኢትዮጵያዊ የእግዳ አቀባበል ስነምግባር ለመቀበል መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.