መጪዎቹን የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት አከባበር በተመለከተ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ መስከረም 10 ቀን 2018ዓ.ም
መጪዎቹን የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት አከባበር በተመለከተ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ መስከረም 10 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶቸ ክንፍ እና ከቦሌ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማኅበር ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ውይይት በዓላቱ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ከወጣቶች በሚጠበቀው ሚና ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አሰፋ በውይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት የክፍለ ከተማው ወጣቶች የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ መንገዶች የነቃ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ ዘንድሮም የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት እሴታቸውን ጠብቀው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ የተለመደ ንቁ ተሳትፏቸውን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ በዓላቱ የአብሮነት፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት በዓላት መሆናቸውን ያወሱት ኃላፊው፣ በዓላቱ በሰላም እንዳይከበሩ በጸረ ሰላም አካላት የሚደረጉ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን ለማክሸፍ የወጣቶች ሚና ግንባር ቀደም እንደሆነ አክለው አስገንዝበዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶቸ ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ሄለን ለገሠ በበኩሏ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገልጻ፣ መጪዎቹ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ በሚደረገው እንቅስቃሴ በሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ ወጣቶች እና የወጣቶች አደረጃጀቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝባለች፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.