የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ሀላፊነታችንን እንወጣለን።
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ሀላፊነታችንን እንወጣለን። የመዲናዋ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች መስከረም 12ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ከወጣቶችና ከስፖርት ቤተሰቦች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ አከባበር ዙሪያ ከብሎክ ጀምሮ ከ500ሺህ በላይ ከሚሆኑ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል። የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ለእኛ ኢትዮጵያን መለያ የሆኑ እና የፍቅር ፣ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት መገለጫ በዓት መሆናቸውን አቶ በላይ ተናገረዋል። በዓላቱን ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አቶ በላይ አሳስበዋል። የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በ UNESCO በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገቡ በመሆናቸው በርካታ እንግዶችና ቱሪስቶች በዓላቱን ለማክበር ወደ መዲናችን ሲመጡ የመዲናዋ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች በፍፁም ኢትዮጵያዊ እሴት መቀበል እና ማስተናገድ እንዳለባቸው አቶ በላይ አሳውቀዋል። የውይይቱ መነሻ ሰነድ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዘዳንት የሆኑት ወጣት መለሰ አባተ የቀረበ ሲሆን በዓላቱ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ዘንድሮ የሚከበሩት የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት የህዳሴ ግድብን አጠናቀን ባስመረቅን ማግስት የሚከበሩ በመሆናቸው በተለየ እና በድምቀት እንደሚከበሩ የተናገሩት ወጣት መለስ እንደ ሀገር በቀጣይ ለመስራት የታቀዱ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ ወጣቶች ተሳትፎቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.