የኢሬቻ በዓል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን ጠ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የኢሬቻ በዓል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በመዲናዋ በሰላም ለማክበር ከኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

የኢሬቻ በዓል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በመዲናዋ በሰላም ለማክበር ከኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ። መስከረም 13 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ወጣቶችና ስፖሮት ቢሮ የኢሬቻ በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም ለማክበር ከኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የኢሬቻ በዓል የፍቅር የሰላም የአብሮነት የወድማማችነት እና የእትማማችነት መገለጫ በዓል በመሆኑ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ገልፀዋል። የኢሬቻ በዓል በዩኒስኮ በማይዳሰሱ ቅርስነት የተመዘገበ የሁሉም የኢትዮጵያን መገለጫ በዓል መሆኑን የተገናገሩት አቶ በላይ በዓሉን ለማክበር ከጎራባች ከተማች ጨምሮ በርካታ እንግዶች እና ቱሪስቶች ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ወደ መዲናዋ የሚመጡ በመሆኑ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በሀገራዊ ልማትና ሰላም ላይ በቅንጅት እንደሚሰሩ ያስተወሱት አቶ በላይ እንደነዚህ አይነት በዓላት የወጣቶችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩ እና የባህል ልውውጥ የሚያደርጉባቸው ናቸው ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮችም የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በሚያጠናክር መልኩ በሰላም ለማክበር በየደረጃው ከወጣቶች ጋር ውይይት መካሄዱን ጠቅሰዋል። የኢሬቻ በዓል የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ መጠን በዓሉ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ቱፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። በነገው እለትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ ከ5ሺህ በላይ ወጣቶች በኢሬቻ አከባበር ዙሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ተገኝተው ውይይት የሚያደርጉ መሆኑን በመድረኩ ተመላክቶል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.