የአንድነት፣የፍቅር፣የይቅርታ፣አብሮነት፣ የምስጋና...

image description
- ውስጥ supporter    0

የአንድነት፣የፍቅር፣የይቅርታ፣አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ እሴቶች የሚገለጹበት በዓላትን ለመጪው ትውልድ ማሻገር የወጣቱ ትውልድ ኃላፊነት ነው/ አቶ በላይ ደጀን/

የአንድነት፣የፍቅር፣የይቅርታ፣አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ እሴቶች የሚገለጹበት በዓላትን ለመጪው ትውልድ ማሻገር የወጣቱ ትውልድ ኃላፊነት ነው/ አቶ በላይ ደጀን/ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በድምቀት እንዲከበሩ የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ ወጣቶች ውይይይት እያካሄዱ ይገኛሉ። በውይይቱ ላያ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የአንድነት፣የፍቅር፣የይቅርታ፣አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ እሴቶች የሚገለጹበት በዓላትን ለመጪው ትውልድ ማሻገር የወጣቱ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል። አዲስ አበባ የሚከበረው ኢሬቻ ሆራ-ፊንፊኔ እና ቢሾፍቱ የሚከበረው ኢሬቻ-ሆራ-አርሰዲ በአንድነት፣በሰላም እንዲከበሩ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ በላይ በዓላቱ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸው ሳይለቁ በሰላም እንዲከበሩ ሚናቸውን እየተወጡ ለሚገኙ ለአዲስ አበባ ወጣቶች እና ለሸገር ከተማ ወጣቶች፣ ቄሮ፣ ቄሬ እና ፎሌዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መስቀል እና የገዳ ሥርዓት በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል/ዩኔስኮ/ የዓለማችን የማይዳሰስ የኢትዮጵያ ወካይ ቅርስ መዝገብ ሥር የሰፈሩ ሀብቶቻችን ናቸው ያሉት አቶ በላይ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ እሴቶች የሚገለጹበት በዓላትን ለመጪው ትውልድ ማሻገር የወጣቱ ትውልድ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን ላሸጋገረው ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል መሆኑን ያወሱት አቶ በላይ ማህበረሰቡ ካለምንም ልዩነት የሚከበር የአብሮነት መገለጫ በዓል የሆነውን ኢሬቻ በተለመደው የወንድማማችነት እና በእትማመችነት መንፈሰ ማክበር ይገባል ብለዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.