እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን እምነት ተከታዮች ፣ ለከተማችን ወጣቶች እና የስፓርት ቤተሰቦች እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረስን !!! መስቀል የተራራቁ የሚቀራረቡበት ፣የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ጥላቻ በፍቅር፣ ሞት በሕይወት፣ ጨለማ በብርሃን የሚተካበት ዓመቱን ሙሉ በሰላም ለመኖር የሚያስችል ብርሃን የሚለኮስበት ታላቅ በዓል ነው። የመስቀል ደመራ በዓል የከተማችን፣የአገራችን ብሎም የዓለም በዓል እንደመሆኑ መጠን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ- ስርዓቱን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ። በድጋሜ እንኳን ለብርሐነ የመስቀሉ አደረሳችሁ!! አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ መስከረም 2018 ዓ/ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.