ኢሬቻ: ለሀገር ማንሰራራት!
ኢሬቻ: ለሀገር ማንሰራራት!
#IRREECHA: Olka' insa Biyyaaf ! የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማጠቃለያ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብር ተካሄደ። መስከረም 22 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብር በኮየ ፈጬ አደባባይ አካሄደ። ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ጉዬ ገልገሎን ጨምሮ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ ነዎሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል። ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት መገለጫ በዓላችን በመሆኑ በድምቀት እንዲከበርና እሴቱ ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ወጣቶችን የስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታቸንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አቶ በላይ ደጀን ተናግረዋል። ኢሬቻ በዓል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት( UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የገዳ ስርዓት አካል በመሆኑ በዓሉን ለማክበር በርካታ እንግዶች እና ቱሪስቶች ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በኢትዮጵያዊ የእንግዳ ተቀባይነት ስነ ምግባር በመቀበል ማስተናገድ እንደሚገባ አቶ በላይ አሳስበዋል። የኢሬቻ በዓልን በድምቀት እና በሰላም እንዲከበር ለማድረግ፤ የሚመጡ እንግዶችን የሚቀበሉ እና የሚያስተናግዱ ከ500ሺህ በላይ የመዲናዋ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች መዘጋጀታቸውን የቢሮ ሀላፊው ገልፀዋል። የሸገር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ጉዬ ገልገሎ በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በአማረና በደመቀ መልኩ ለማክበርና ለማስተዋወቅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የሸገር እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦችም የኢሬቻ በዓልን በድምቀት ለማክበር እና እንግዶችን ለመቀበል በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
ኢሬቻን ለማክበር ወጣቶችን ያሳተፈ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.