ኢሬቻ ከባህላዊ ትውፊቱ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ኢሬቻ ከባህላዊ ትውፊቱ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ኢሬቻ ከባህላዊ ትውፊትና ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ለከተማ እድገት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ መላው ሰራተኛ ጋር በመሆን የ2018 የኢሬቻ ባህልን በተለያዩ ዝግጅት አክብሯል 'ኢሬቻ ለማንሰራራት' በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መድረክ ላይ የቢሮ የስራ ኃላፊዎች መላው ሰራተኞች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብሯል በርካታ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦች አብረው የሚያከብሩት ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ምልክት ነው ያሉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የዕድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብረው የቆየ በዓል መሆኑን አውስተዋል። የፍቅርና የሰላም ተምሳሌት የሆነው ኢሬቻ በዓልን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባጠናቀቅንበት ወቅት መካሄዱ ለየት ያደርገዋል አቶ ዳዊት በዓሉ ከመላዉ ዓለም የሚመጡ ከሰባት ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አስታውሰው ሁሉም ሰራተኛ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል ከአጎራባቹ የሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በልዩ ሁኔታ ለማክበር በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በፍቅር ማስተናገድ እንደሚገባ አመላክተዋል ኢሬቻ አስመልክቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ገለጻ ያደረጉት ወይዘሮ ስንት ነዋይ የበዓሉ መከበር ዋና ዓላማ አገራዊ አንድነትን ለማጽናት እና ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር ነው ብለዋል ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!! https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 https://addisyouthandsport.gov.et/ https://www.tiktok.com/@youth.sport.bureau... https://t.me/youthsport2014 https://youtube.com/@a.ayouthsport2017?si=RgfuzOvKZiC54-Fm
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.