የ2018ዓ.ም የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የ2018ዓ.ም የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በይፋ ተጀመረ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ/ም

የ2018ዓ.ም የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በይፋ ተጀመረ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት የ2018ዓ.ም የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር በይፋ አስጀምረዋል። ብቁ ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን በሚል መሪ ቃል በዳግማዊ ምንሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው የብዙሐን አካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ መላው የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ጨምሮ የክፍለ ከተማ አመራሮች የትምህርት ቤቱ ማሕበረሰብ አባላትና ተማሪዎች ተሳትፈዋል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ከመግባታቸው በፊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን ማስለመድ ለመማር ማስተማር ሂደቱ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት አቶ ዳዊት ከለውጡ ወዲህ ለስፓርት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት በየትምህርት ቤቱ ማዘውተርያ ስፍራዎች መገንባታቸው ትምህርት ቤቶች የተተኪዎች መፍለቂያ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን የዘመናዊ ትምህርት ከመሆኑ ባሻገር ለአገራችን በርካታ ስፓርተኞችን ማፍራቱን ያስታወሱት አቶ ዳዊትየማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ተማሪዎችን ንቁና ብቁ ዜጋ ለመሆን እንደሚያስችላቸው አስገንዝበዋል የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘወትር ማክሰኞ እና ሐሙስ ጠዋት እንደሚካሄድ ያስታወቁት አቶ ዲናኦል አስታውሰው ተማሪዎች ስርአት መስራት ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር ተተኪ ስፓርተኛ ለመሆን እንደሚያስችል ገልጸዋል ስፓርት ለሁለንተናዊ እድገት ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ማፍሪያ አይነተኛ መንገድ ያሉት አቶ ዲናኦል ከስፓርት ቢሮ በቅንጅት የተጀመሩ ስፓርታዊ ውድድሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአስረ አንዱም ክፍለ ከተማ ዛሬ መጀመሩን የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት ማስፋፋያ ተሳትፎ ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.