የመዲናዋ ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የመዲናዋ ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሮው ትኩረት አድርጎ ይሰራል። አቶ በላይ ደጀን

የመዲናዋ ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሮው ትኩረት አድርጎ ይሰራል። አቶ በላይ ደጀን መስከረም 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 8ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የኪነ ጥበብ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በብሔራዊ ቲያትር በለውጡ የተለወጠ ወጣት በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ የመዲናዋን ወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሮው ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የውድድሩ አላማም ወጣቶች በኪነጥበብ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት የሚያወጡበት፤ እርስ እርስ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ህብረ_ብሔራዊ አንድነታቸውን የሚያጎለብቱበት እና ተተኪ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለማፍራት መሆኑን አቶ በላይ ገልፀዋል። በከተማ አስተዳደሩ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መካከተል 83 ፐርሰንቱ ወጣቶች መሆናቸውን ያሳወቁት አቶ በላይ ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ተላቀው ስራ ፈጣሪ እየሆኑ መምጣታቸውንም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መክብብ ወ/ሀና በበኩላቸው ለወጣቶች ምቹና ዘመናዊ የሆኑ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በከተማ አስተዳደሩ እንደሚገኙ እና 18 የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በኪነ ጥበብ ክበባት ተደራጅተው ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች በተለያዩ የኪነጥበብ ውድድሮች በመሳተፍ የከተማቸውን ብሎም ሀገራቸውን ስም እያስጠሩ መሆኑን አሳውቀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.