8ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የኪነጥበብ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

8ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የኪነጥበብ ውድድር ተጠናቀቀ

8ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የኪነጥበብ ውድድር ተጠናቀቀ ኢትዮጵያዊነት እና ሜንዝ የኪነጥበብ ቡድኖች በባህል ውዝዋዜና በዘመና ዳንስ አሸናፊ ሆነዋል። መስከረም 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በለውጡ የተለወጠ ወጣት በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ቲያትር ያዘጋጀው 8ኛውን ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል የኪነጥበብ ውድድር ተጠናቆል። ለሁለት ወራት ሲካሄድ በቆየውና ዛሬ ፍፃሜውን ባገኝው የኪነጥበብ ውድድር በባህላዊ ውዝዋዜ የ ኢትዮጵያውነት ባህል የኪነጥበብ ቡድን ከቦሌ ክፍለ ከተማ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ሻሎም የባህል የኪነጥበብ ቡድን ሁለተኛ አንድ ኢትዮጵያ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በዘመናዊ ዳንስ በተካሄደው ውድድር ሜንት ዘመናዊ ዳንስ ቡድን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ጥያቄ ዘመናዊ ዳንስ የኪነጥበብ ቡድን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ እና ጊዮን የዘመናዊ ዳንስ ቡድን ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በውድድሩ በባህላዊ ውዝዋዜ እና በዘመናዊ ዳንስ ውድድር ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ የኪነጥበብ ቡድኖች የ150ሺህ፣ የ125ሺህ እና 100ሺህ የብር ሽልማት እንደየደረጃቸው ተበርክቶላቸዋል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.