19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ በፍፁም...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላትን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን አመሰገኑ።

19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ያደረጉ አካላትን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን አመሰገኑ።

ጥቅምት 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በፍፁም በስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የማኔጅመት አባላትን፣ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚዎችን ፣ የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን፣ የስፖርት ክለብ አመራሮችን፣ ደጋፊዎችን፣ አስጨፋሪዎችን፣ ስቲዋርዶችን እና ደኞችን እና የስፖርት ቤተሰቦችን የአዲስ አበባ ከከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የህዳሴ ዋንጫ የመዲናዋ መለያ መሆኑን የተናገሪት አቶ በላይ ውድድሩ በድምቀት እና በሰላም እንዲካሄድ ከስፖርት ክለብ አመራሮች፣ ደጋፊዎች፣ አስጨፋሪዎች፣ ስቲዋርዶች እና የስፖርት ባለሙያዎች ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ መካሄዱን ተናግረዋል።

19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የህዳሴ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከመስከረም 18 እስከ ጥቅምት 02 በአዲስ አበባ ስታድየም ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.