ቅዱስ ጊዮርጊስ የ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የህዳሴ ዋንጫ ሻምፒዮና ሆነ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የህዳሴ ዋንጫ ሻምፒዮና ሆነ

ጥቅምት 02 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የህዳሴ ዋንጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ፍፃሜውን ያገኝ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 2 ለ1በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮና መሆን ችሏል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ የማሸነፊያ ግቦችን አሸናፊ ጌታቸው እና አዱሱ አቱላ ሲያስቆጥሩ የመቻልን ብቸኛ ጎል ሄኖክ ዮሐንስ በራሱ ላይ አስቆጥሯል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮና መሆኑን ተከትሎ የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ ሲበረከትለት መቻል የብር ሜዳልያ ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል።

ሽልማቱን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር መኪዩ መሐመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን እና የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ ሰጥተዋል።

በርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ መስከረም 18 ጀምሮ በስድስት ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው 19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የህዳሴ ዋንጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ፍፃሜውን አግኝቷል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.