ቢሮው በፒኮክ መናፈሻ የቴኒስ ሜዳ ግንባታ ለማስጀምር በተጋጀው ዲዛይን ላይ ውይይት አካሄደ
ቢሮው በፒኮክ መናፈሻ የቴኒስ ሜዳ ግንባታ ለማስጀምር በተጋጀው ዲዛይን ላይ ውይይት አካሄደ
ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመተባበር በፒኮክ መናፈሻ የቴኒስ ሜዳ ግንባታ ለማስጀምር በተጋጀው ዲዛይን ላይ ውይይት አካሄደ
ዲዛይኑ ሂስ ለማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የሁለቱም ተቋም ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙዎች ተገኝተዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ለሁሉም ስፖርት ዘርፍ ለሰጠው ትኩረት በፒኮክ ሊገነባ የታሰበው ቴኒስ ሜዳ ማሳያ ነው ያሉት የወጣቶች እናስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ግንባታ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድያ ሟላ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
በተዘጋጀው ዲዛይን ላይ የተሰጠው ሂስ በማስተካከል በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው እንደሚጀመር የገለጹት አቶ ዳዊት ደረጃውን የጠበቀ የቴኒስ ሜዳ ግንባታ መከናወኑ ለውድድር እና ለልምምድ ሰፊ ዕድል እንደለው አመላክተዋል፡፡
በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እንደተጀመረ የሚነገርለት የኦሎምፒክ ስፖርት የሆነው የሜዳ ቴኒስ አሁን ላይ በአዲስ አበባ በክልሎች እና በሁሉም የዓለም ማዕዘን እየተዘወተረ የሚገኝ ተወዳጅ ስፖርት ነው፡፡
ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!!
??https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
https://addisyouthandsport.gov.et/
https://www.tiktok.com/@youth.sport.bureau...
https://youtube.com/@a.ayouthsport2017?si=RgfuzOvKZiC54-Fm
Comments
ምንም አልተገኘም.






አስተያየቶችዎን ይተዉት.