ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና በሁለት ማንዋሎች ላይ ውይይት አካሄደ

ቢሮው የበጀት አመቱን የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና በሁለት ማንዋሎች ላይ ውይይት አካሄደ

ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችን ስፖርት ቢሮ የስፓርት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ሪፓርት፣በሁለተኛ የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ እና የዳኝነት እና የአሰልጣኝነት መተግበርያ ማናዋል ላይ ውይይት አካሂዷል።

በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተካሄደው ውይይት ላይ የስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ የፌዴሬሽን የፅ/ቤት ኃላፊዎችና የክፍለ ከተማ የስፖርት ዘርፍ ቡድን መሪዎች ተሳትፈውበታል።

በ2017 በጀት አመት በአገር አቀፍ ምዘና በስፖርት ዘርፍ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ውጤታማ መሆኑ ትልቅ ስኬት ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የዳኝነትና የአሰልጣኝነት መተግበርያ ማንዋሎችን ማዳበር እንደሚገባ እና በአዲስ አበባ ከተማ አዘጋጅነት የሚካሄደው 2ኛው የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በላፈው ሩብ ዓመት በርካታ ውጤቶች ለመመዝገባቸው አስቻይ ሁኔታዋች መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ ዳዊት ለጊዜ ዋጋ በመስጠት በዝግጅት ምዕራፍ መከናወን ያላባቸው ተግባራት በአስቸኳይ እንዲጠናቀቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማውን ስፓርት እንደሚመራ አካል በብቃት እና በቅንጅት መምራት እንደሚያስፈልግ ያመላከቱት አቶ ዳዊት ስፓርቱን በሳይንሳዊ መንገድ እየመራን ተተኪ ስፖርተኞችን በጥራትና በብዛት ለማፍራት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል

በሁለተኛው የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ዕቅድ ላይ ገለጻ ያደረጉት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ በአንደኛው ኦሎምፒክ የተገኘውን ድል ለመድገም ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዋች መሰራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

የ2018 አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ ያደደረጉ የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት ማስፋፋያ ተሳትፎ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በስፓርት ዘርፍ በተከናወኑ አበይትና ዋና ዋና ተግባራት ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።

የሁሉም ፌዴሬሽኖች የዳኝነት እና የአሰልጣኝነት ማስተግበርያ የጥናት ሰነድ ላይ ገለጻ ያደረጉት የራስ ኃይሉ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ በቀለ ውጤታማ የአሰለጣጠን ሂደትን ውጤታማ ለማድረግ አገር አቀፍ ልምዶች እና ዓለም አቀፍ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዋች ስፓርቱን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ሚናቸውን እንደሚወጡ ገልጸው የሚከፈተው ፕሮጀክቶች ውጤት ቢለካ ሁሉንም ስፓርት ለማስፋፋት በትኩረት ቢሰራ ፌዴሬሽኖች በክፍለ ከተማ ወርዶ የመደገፍ ስራ ቢያጠናክሩ የሚሉ ምክር ሃሳቦችን ሰጥተዋል።

አቶ ዳዊት በሰጡት የስራ አቅጣጫ በልዩ ልዩ ንቅናቄዋች የባህል ስፓርት የአካል ጉዳተኞች ውድድር የተማሪዋች ሊግ ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ አሳስበው ጥቅምት 15 በሚጀምረው የኦሎምፒክ ውድድር አቀበባል ጨምሮ ሁሉም እንቅስቃሴ በቅንጅት እንዲሰራ አሳስበዋልወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!!

📱https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

🔤https://addisyouthandsport.gov.et/

📱https://www.tiktok.com/@youth.sport.bureau...

💬https://t.me/youthsport2014

🌐https://youtube.com/@a.ayouthsport2017?si=RgfuzOvKZiC54-Fm

Facebook (https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219)

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.