ቢሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰና በድምቀት በመዲናዋ እንዲካሄድ የሚያስችል ውይይt አካሄደ።
ቢሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ በመዲናዋ እንዲካሄድ የሚያስችል ውይይት ከስፖርት ክለብ ደጋፊዎች እና ስቲዋርዶች ጋር አካሄደ።
ጥቅምት 06 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰና በድምቀት በመዲናዋ እንዲካሄድ የሚያስችል ውይይት ከስፖርት ክለብ ደጋፊዎች፣ ስቲዋርዶችና አስጨፋሪዎች ጋር አካሄደ።
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ሼር ካምባኒ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፍን ጨምሮ የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።
19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ ካለምንም የፀጥታ ችግር በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ ለመጠናቀቁ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች፣ ሰቲዋርዶች እና የአስጨፋሪዎች ሚናቸው የጎላ እንደነበር አቶ በላይ ተናግረዋል።
ከ6 አመታት በሆላ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ በመዲናዋ መካሄዱ የስፖርት ኢንቨስትመንትን በከተማዋ ከማሳደግ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት የተናገሩት አቶ በላይ ውድድሩ በፍፁም በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄድ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች እና ስቲዋርዶች ከአወዳዳሪው እና ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ሥራ አሰኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፍ በበኩላቸዉ ሊጉን ተወዳጅና ውጤታማ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለስፖርት ክለብ ደጋፊዎች እና ስቲዋርዶች በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ የስፖርት ሳይንስ ሙሁር በሆኑት በዳ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ስልጠና ተሰጥቷል።
የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ውድድር ጥቅምት 8 በአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚጀመር ይታወቃል።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
https://addisyouthandsport.gov.et/
https://www.tiktok.com/@youth.sport.bureau...
https://youtube.com/@a.ayouthsport2017?si=RgfuzOvKZiC54-Fm
Facebook (https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219)
Comments
ምንም አልተገኘም.






አስተያየቶችዎን ይተዉት.