ቢሮው የስፖርት ስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አስመልክቶ ስልጠና መስጠት ጀመረ
ቢሮው የስፖርት ስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አስመልክቶ
ስልጠና መስጠት ጀመረ
ጥቅምት 7 ቀን2017 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከክፍለ ከተሞች ጋር በመቀናጀት የስፖርት ስልጠና ፍላጎትና ዳሰሳ ጥናት አስመልክቶ ያዘጋጀውን ስለጠና መስጠት ጀመረ፡
የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ እና የስልጠና ፋይዳ ጥናት አዘገጃጀት ዙሪያ ባተኮረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ጉለሌ ቂርቆስ, አራዳ በአቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በሌሎች ክፍለ ከተሞችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡
በበጀት አመት የሚጠኑ የጥናትና የምርምር ስራዎች ዉጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከማዕከል አስከ ወረዳ ለሚገኙ የሴክተሩ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ያስታወሱት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ በራስ አቅም የሚሰጡ ስለጠናዎች የስፖርት ዘርፉን የሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ እንደሚያስችሉ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው የስፖርት ዘርፍ ባለሙያዎች ተግባሮቻቸውን በውጤታማነት ለመምራትና እንደሚግዝ የገለጹ አቶ ጎሳዬ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ያስችል ብለዋል
ጥንካሬዎችን የሚያስቀጥሉ እና ውጤታማነትን ከፍ የሚያደርጉ ስልቶችን ለመቀየስ የዳሰሳ ጥናት ስልጠናዎች እንደሚያግዙ የገለጹት አቶ ጎሳዬ አዳዲስ አሰራሮችን በመንደፍ ተሞክሮዎችን በማስፋት ከክፍለ ከተማ ስፖርት ቡድኖች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በዳሰሳ ጥናቱ የሚገገኙ አደዲስ ግኝቶች ተግባርላይ የሚውሉበት አሰራር እንደሚዘረጋ ያመላከቱት አቶ ጎሳዬ በ2018 በጀት አመት በመረጃ አሰባሰብ፣በመረጃ ትንተና የጥናት ምንነት ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል
የውይይቱ ተሳታፊዎች በርካታ ምክረ ሀሳቦችን የለገሱ ሲሆን በሁሉም ስፖርት አይነት ስለጠናዎችን በመስጥ ውጤታማ በሆንበት ስፖርት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
በአዲሱ በበጀት አመት ዘርፉ 13 በራስ አቅም ጥናቶች ለማስጠናት በእቅድ ይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡
ቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!!
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
https://addisyouthandsport.gov.et/
https://www.tiktok.com/@youth.sport.bureau...
https://youtube.com/@a.ayouthsport2017?si=RgfuzOvKZiC54-Fm
Facebook (https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219)
አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . | Addis...
አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau ., Addis Ababa. 21,634 likes · 5,700 talking about this. ይጎ
Facebook (https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219)
አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . | Addis...
አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau ., Addis Ababa. 21,634 likes · 5,700 talking about this. ይጎብኙን
Comments
ምንም አልተገኘም.




አስተያየቶችዎን ይተዉት.