የሸገር ደርቢ ጨዋታ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄድ ሀላፊነታችንን እንወጣለን፦ የሁለቱ ክለብ አሰጨፋሪዎች
የሸገር ደርቢ ጨዋታ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄድ ሀላፊነታችንን እንወጣለን፦ የሁለቱ ክለብ አሰጨፋሪዎች
ጥቅምት 09 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አስጨፋሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ከአቶ በላይ ደጀን ጋር ዛሬ በማካሄደው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
የሁለቱ ክለብ አስጨፋሪዎች ዛሬ የሚካሄደው የሸገር ደርቢ ጨዋታ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄድ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ በላይ ደጀን ከስድስት አመታት በሆላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ መዲናዋ መመለሱ ለከተማዋ የስፖርት እድገት እና የወጣቶችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር ሚናው የጎላ በመሆኑ በመዲናዋ የሚካሄዱ ሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች ካለምንም የፀጥታ ችግር በፍፁም በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄዱ ሁሉም አካል ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የ2018 ሲቢኢ ኢትዮጵያዊ ፕሪሚየር ሊግ የሸገር ደርቢ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ከቀኑ 9 ስዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.