ቢሮው የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
ቢሮው የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችን ስፖርት ቢሮ የወጣት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ሪፓርት፣ የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ውይይት እና የቀጣይ ሦስት ወራት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተካሄደው መድረክ ላይ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ስራ አስኪያጆች የሁሉም ክፍለ ከተማ የወጣት ዘርፍ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ የወጣቶች እና ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎቸ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል በወጣት ዘርፍ የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎችን የማስፋትና አጠናክሮ የማስቀጠል ስራ ለአገልግሎት አሰጣጡ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ክብርዓለም በበጀት ዓመቱ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን በመፍተት የወጣቱን እርካታ የማረጋገጥ ሥራ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል በቢሮው የተጀመረው የውጤታማነት ስራ ለማስቀጠል በየደረጃው ካሉ አመራር እና ሰራተኛ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ያወሱት አቶ ክብርዓለም በቀጣይ ተቋማትን የማበረታት እና ዕውቅና የመስጠት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ በወጣት ዘርፍ የልማት ዕቅድ እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ላይ ገለጻ ያደረጉት የወጣት ስብዕና መገንቢያ ልማት ቡድን ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ምትኩ ዋና ዋና ተግባራትን ለማስፈጸም በሚሰሩ ስራዎችን አመላክተው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ ዋና ዋና ስትራቴጂክ ጉዳዮችና አፈጻጸማቸውን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች፣ የመፍትሔ እርምጃዎችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን የወጠቶች ግንዛቤ እና ንቅናቄ ቡድን መሪ አቶ ንጋቱ አየለ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!! https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 https://addisyouthandsport.gov.et/ https://www.tiktok.com/@youth.sport.bureau... https://t.me/youthsport2014 https://youtube.com/@a.ayouthsport2017?si=RgfuzOvKZiC54-Fm Facebook Facebook (https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219) አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . | Addis... አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau ., Addis Ababa. 21,634 likes · 5,700 talking about this. ይጎ Facebook (https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219) አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . | Addis... አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau ., Addis Ababa. 21,634 likes · 5,700 talking about this. ይጎብኙን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.