2ኛውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታውች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ አስጀምረውታል። ጥቅምት 15 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
2ኛውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታውች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ አስጀምረውታል።
ጥቅምት 15 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
2ኛውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ አስጀምረውታል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ መንግስት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለስፖርት ሁለንተናዊ እድገት በሰጠው ልዩ ትኩረት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ በርካታ መሰረተ ልማቶችን አሞልቶል ብለዋል።
ወጣቶች የተፈጠረላቸውን መልካም እድል በመጠቀም ተወዳዳሪ እና አሸናፊ ስፖርተኛ ለመሆን ጠንክሮ መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ከንቲባዋ አሳስበዋል።
ስፖርት ከውድድር ባለፈ አንድነት፣ አብሮነት፣ ፣ወድማማችነት፣ የእህትማማችነት የምናጠናክርበት የሰላም መድረክ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተወዳዳሪዎች በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ተወዳዳሪ እና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመፍጥ እንዲሁም በአካል እና በአእምሮ የዳበረ መህበረሰብን ለመገንባት መንግስት ለስፖርቱ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቷ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ በጥራትና በብዛት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እየተገነቡ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስቴሯ ሌሎች ክልሎች አዲስ አበባ ልምድ ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ዳ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው በ2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች እሎምፒክ ጨዋታ 12 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.