የካ ክፍለ ከተማ ከ70 በላይ ቀጣሪ ድሮጅቶች የተሳተፉበት በአንድ ጀንበር 1000 የስራ እድል ፈጠራ አወደ ርዕይ አዘጋጀ።
የካ ክፍለ ከተማ ከ70 በላይ ቀጣሪ ድሮጅቶች የተሳተፉበት በአንድ ጀንበር 1000 የስራ እድል ፈጠራ አወደ ርዕይ አዘጋጀ። ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው ከ70 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች የተሳተፉበት በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል ፈጠራ አውደ ርዕይ የከተማ እና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተካሄደ። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ እንደገለፁት ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶች እና ሴቶችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው በበጀት አመቱ ከ350ሺ በላይ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ከተማ አስተዳደሩ ያስቀመጠውን አቅጣጫ በመከተል እና በፍጥነት በመተግበር የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል በመፍጠር ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ግንባር ቀደም ሆኖ ከፍታውን መውሰዱን አቶ አስፋው ገልፀው ለአስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትፍሩ በበኩላቸው ወጣቶች የሚያገኟቸውን ዕድሎች በአግባቡ በመጠቀም እና ራሳቸውን በመለወጥ ሀገራችን የጀመረችውን የማንሰራራት ጉዞ ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ እንደገለፁት ባለፉት የለውጥ አመታት ከተማ አስተዳደሩ ክህሎትን መሰረት ያደረገ ተጨባጭ የስራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አንስተው እንደ የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደርም ባለፉት ሶስት ወራት ከ8000 በላይ የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልፀው በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል ለመፍጠር አስተዳደሩ ያመቻቸውን ዕድል ወጣቶች እና ሴቶች በአግባቡ እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፈው በቀጣይም በዘርፋ ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አፅንኦት ሰጥተዋል። የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት በበኩላቸው በዛሬው ዕለት በተካሄደው በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል ፈጠራ ዓውደ ርዕይ ላይ ከ21ሺ 800 በላይ የስራ ዕድል የሚፈጥሩከ70 በላይ ድርጅቶች መሳተፉቸውን ጠቅሰው ለሁለት ቀን በሚቆየው የስራ ዓውደ ርዕይ ላይ ከ2000 በላይ የስራ ዕድል ለመፍጠር ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል። የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል የስራ ዕድል ፈጠራ አውደ ርዕይ ለ2 ቀን የሚቆይ ሲሆን የዚህ ዕድል ተጠቃሚዎች የስራ ፈላጊ ምዝገባ ተመዝግበው የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ የቆዩ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በመድረኩ የስራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጥቷል። በመርሃ ግብሩ ላይ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ፣የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላናን ጨምሮ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እና አመራሮች ተገኝተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.