በቦሌ ክፍለ ከተማ ''አዲስ አቅም፤ አዲስ እድል ለወጣቶች!'' በሚል መሪ ሀሳብ በወጣቶች በስራ እድልና በመንግስት ማዕቀፍ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ''አዲስ አቅም፤ አዲስ እድል ለወጣቶች!'' በሚል መሪ ሀሳብ በወጣቶች በስራ እድልና በመንግስት ማዕቀፍ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። ጥቅምት 18 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ ከአስራ አንዱም ወረዳዎች ለተውጣጡ ወጣቶች በሥራ እድልና በመንግሥት የድጋፍ ማዕቀፍ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የማይንድ ሴት ሥልጠና ተሰጥቷል። ''አዲስ አቅም፤ አዲስ እድል ለወጣቶች!'' በሚል መሪ ሐሳብ በተሰጠው በዚህ ሥልጠና ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የሰው ሀይል፣ ሀብትና ፀጋዎች በመጠቀም የሚቻል በመሆኑ ወጣቶች ሀገራችን ባላት ሀብትና በተመቻቸላቸው የሥራ ዕድል ተጠቅመው እራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ሀገራቸውን ከድህነት ለማውጣት በቅድሚያ አመለካከታቸውን መቀየርና በተግባር ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዷለም አሰፋ በበኩላቸው እንደተናገሩት አስተሳሰብ ከተቀየረ ብቁ፣ የተማረና የፈጠራ ክህሎት ያለው ዜጋ ካለ ሀገር ትለወጣለች፣ ልማትም ይፋጠናል ለዚህ ደግሞ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ወጣቶች ላይ የሚታይ ለውጥ እንዲመጣ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገለጸው የማይንድሴት ስልጠናው ለወጣቶች የሚታይ ለውጥ የሚያመጣ፣ እይታን የሚያስተካክል ትርጉም ያለው ህይወት እንዲመሩ የሚያስችል ፋይዳ ያለው በመሆኑ ስልጠናው የወጣቱን አስተሳሰብ፣ አመለካከትና የእውቀት አድማስ ይበልጥ እንዲያሰፋ በየጊዜው ስልጠና እንደሚሰጥም ገልፀዋል። ወጣቶች ሁልጊዜ ብልህና አስተዋይ የሆነ አስተሳሰብን በመላበስ የይቻላል መንፈስን በማጎልበት ስራ ፈጣሪና የስራ ባለቤት በመሆን ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው በስልጠናው ላይ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል። በስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው በቂ እና ጠቃሚ ግንዛቤን ስለመያዛቸውና ወደ ተግባር ለመቀየር ስለመዘጋጀታቸው ገልጸው በቀጣይ መሰል የስልጠና መድረኮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.