በመደመር መንግስት መጽሐፍ ዙሪያ የወጣቶች የፖናል ውይይት ተካሄደ።
በመደመር መንግስት መጽሐፍ ዙሪያ የወጣቶች የፖናል ውይይት ተካሄደ። ጥቅምት 18 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዳ/ር አብይ አህመድ በተፃፈ የመደመር መንግስት መጽሐፍ ዙሪያ ከከተማው ወጣቶች ጋር ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ ወጣቶች የመደመር መንግስት መፅሐፍን በማንበብ፣ በመገንዘብ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር አሻራቸውን ሊያስቀምጡ እንደሚገባ ተናግረዋል። በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ወጣቶች የማይተካ ሚና እንዳላቸው የገለፁት አቶ ክብረአለም ወጣቶች በመደመር እሳቤ በሀገራቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ፋና ወጊ መሆን አለባቸው ብለዋል። ለፖናል ውይይቱ መነሻ ሐሳብ ለወጣቶቹ አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቅርበዋል። አቶ ዛዲግ ወጣትነት የመሸጋገሪያ የእድሜ እርከን ሳይሆን የነገ ህይወታችንን የምንወስንበት በመሆኑ በአግባቡ በመጠቀም የራሳችንን ብሎም የሀገራችንን የነገ ተስፋ የሚያለመልሙ ስራዎችን ሰርተው የሚያሳልፍበት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። የወጣትነት የእድሜ እንከንን በአግባቡ በመጠቀም የራስ፣ የቤተሰብን፣ የማህበረሰብን፣ የተቆምን ብሎም የሀገርን ነባራዊ ሁኔታ መቀየር እንደሚቻል አቶ ዛዲግ በውይይታቸው በስፋት ገልፀዋል። ወጣቶች በመደመር ፅንሰ ሀሳብ ሀሳባቸውን፣ አላማቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ራዕያቸውን በመደመርና አብሮ ሰርቶ የመለወጥ እሳቤያቸውን በማሳደግ በሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት ላይ በጎ አስተዋጽኦቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባ በፖናል ውይይቱ ላይ ተመላክቷል። በፖናል ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊዎች አቶ ዳዊት ትርፋ እና አቶ ኮብረ አለም ደምሴ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ፕሬዘዳንት ወጣት በረከት ቢርቢሳ እና ከ11ዱም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ ወጣቶች ተሳትፈውበታል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.