አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት መንግስት በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። ክቡር ቀጀላ መርዳሳ
አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት መንግስት በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። ክቡር ቀጀላ መርዳሳ ጥቅምት 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የማጠቃለያ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስታድየም እየተካሄደ ይገኛል። በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የወጣቶችና ስፖርት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስቴር አቶ ቀጀላ መርዳሳ መንግስት አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከመገንባት ጀምሮ ሌሎች የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ለማሞላት እንደሀገር እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ቀጀላ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ልዩ ትኩት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ እንደሀገር ያጋጠመንን የስፖርት ስብራት በመጠገን ለኢትዮጵያ የስፖርት ትንሳኤ ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ሀላፊነቱን እንደሚወጣ ተናግረዋል። ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በከተማ አስተዳደሩ 410 የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ጣቢያዎችን በማቆቆም ከ26ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ19 የስፖርት አይነቶች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ዳ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በሁለት አመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በየአመቱ እንዲካሄድ መወሰኑን ተናግረዋል። በወጣቶች ስፖርታዊ ውድድር ላይ የሚያጋጥመውን የእድሜ ተገቢነት ጉዳይ በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ዳ/ር አሸብር ተናግረዋል። በ2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ የሚሳተፉ ስፖርተኞችን መምረጥ እንደተቻለ ዳ/ር አሸብር ገልፀዋሌ። 3ኛውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታን የትግራይ ክልል እንደሚያዘጋጅ የገለፁት ፕሬዘዳንቱ ከ9ኝ ወራት በሆላ ውድድሩ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.