አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሎምፒክ ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ። ጥቅምት 23 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሎምፒክ ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ። ጥቅምት 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ዛሬ ሲጠቀቅ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሎምፒክ ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 46 ወርቅ ፣ 41 ብር እና 25 ነሐስ በአጠቃላይ 112 ሜዳልያዎችን በኦሎምፒክ ስፖርቶች በመሰብሰብ ውድድሩን በበላይነት አጠናቆል። ኦሎምፒክ እና ኦሎምፒክ ባልሆኑ ስፖርቶች የኦሮሚያ ክልል አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል። የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ለሀገር ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ጨዋታ 12 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፈውበታል። ውድድሩ በ20 የስፖርት አይነቶች የተካሄደ ሲሆን ከ5ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል። በ2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ የሚሳተፉ ስፖርተኞችን በየስፖርት አይነቱ መምረጥ እንደተቻለ ተመላክቷል። 3ኛውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ እንዲያዘጋጅ የተመረጠው የትግራይ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዘጋጅነት አርማውን ተረክቦል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.