2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በአማረና በደመቀ መልኩ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ምስጋና አቅርበዋል።
2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በአማረና በደመቀ መልኩ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ምስጋና አቅርበዋል። ጥቅምት 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በአማረ እና በደመቀ መልኩ ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ያደረጉ አካላትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ አመስግነዋል። ውድድሩ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄ እና አዲስ አበባ ህብረ ብሔራዊት የሰላምና የፍቅር ከተማ መሆኗን ላሳዩ የከተማው ነዋሪዎች፣ አመራሮች፣ የቢሮ ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላት፣ የስፖርት ባለሙያዎችና ቤተሰቦች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የትምህርት ማህበረሰቦች እና ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትን አቶ ዳዊት በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት ከጥቅምት 15 ጀምሮ ለተከታታይ 9 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ መጠናቀቁ ይታወቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.