ቢሮው በልደታ ክፍለ ከተማ የመደመር መንግስት የወጣቶች የፖናል ውይይት አካሄደ። ጥቅምት 24 ቀን 2018ዓ.ም
ቢሮው በልደታ ክፍለ ከተማ የመደመር መንግስት የወጣቶች የፖናል ውይይት አካሄደ። ጥቅምት 24 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በልደታ ክፍለ ከተማ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዳ/ር አብይ አሕመድ በተፃፈው መደመር መንግስት መፅሐፍ ፅንሰ ሀሳብ ላይ ያተኮረ የወጣቶች የፖናል ውይይት አካሄደ። በፖናል ውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ የመደመር መንግስት መፃሀፍ በሀገር በቀል እሳቤዎች የተዋቀረ ለሀገራዊ ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔዎችን ያመላከተ መፅሐፍ ነው ብለዋል። መደመር፣ የመደመር መንገድ ፣ የመደመር ትውልድና የመደመር መንግስት መፅሀፎች ነገን የሚያሳዩና ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቁ ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎሉ መሆናቸውን አቶ ክብረአለም ገልፀዋል። በሌላ በኩል ለፖናል ውይይቱ መነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ሀላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ በበኩላቸው የመደመር እሳቤ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እሳቤ መሆኑን ገልፀዋል። የመደመር መንግስት መፅሀፍ ተግባራትን በቅንጅት በማከናወን ለችግሮች ከራስ የመነጨ መፍትሔ በማስቀመጥ ለሀገር ብልፅግና ለመትጋት የሚያነሳሳ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል። የመደመር መንግስት መፅሀፍ ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣና ለሀገር ብልፅግና እንዲተጋ መንገዶችን ያመላከተ መሆኑን በውይይቱ ተመላክቷል። አቅምን መጠቀም፣ ምዕናብን ከፍ ማድረግ፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ያስገኘው ውጤትና የፖለቲካ ባህልን ማሻሻል በውይይቱ በስፋት የተነሳ ሲሆን ወጣቶች በሀገራቸው ሁለንተናዊ ብልፅግና አሻራቸውን ማስቀመጥ እንዳለባቸው ተጠቁሞል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመደመር መንግሰት የወጣቶች የፖናል ውይይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.