ባለፉት ሶስት ወራት በከተማችን የስራ እድል ከተ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ባለፉት ሶስት ወራት በከተማችን የስራ እድል ከተፈጠረላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል 83 ፐርሰቱ ወጣቶች ናቸው።

ባለፉት ሶስት ወራት በከተማችን የስራ እድል ከተፈጠረላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል 83 ፐርሰቱ ወጣቶች ናቸው። አቶ ዳዊት ትርፉ ጥቅምት 25 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት የእቅድ አፈፃፀምን ሪፖርትን ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች እንዲሁም ከወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ስራ አስኪያጆች ጋር ገመገመ። በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ቢሮው በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት ከዝግጅት ስራዎች በተጨማሪ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማውን የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ውጤታማ ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል። በሩብ አመቱ ከ93ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱት የተናገሩት አቶ ዳዊት በከተማው የስራ እድል ከተፈጠረላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል 83 ፐርሰቱ ወጣቶች ናቸው ብለዋል። እንደሀገር በቀጣይ 10 አመታት አሸናፊ ብሔራዊ ብድን ለመገንባታ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደ አዲስ አበባ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማትን ጨምሮ ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ልዩ ትኩረት ተሰጥቷት እየተሰራ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል። የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ባህላዊ በዓላት እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ አስተዋጽኦቸው ከፍተኛ እንደነበረ ም/ቢሮ ሀላፊው ገልፀዋል። በበጀት አመቱ ቀጣይ ወራት የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነት ለማረገጥ እንዲሁም በስፖርት ሁለንተናዊ ልማትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተያዙ እቅዶችን ለማሳካት ሁሉም አካል ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አቶ ዳዊት አሳስበዋል። የቢሮውን የ2018 በጀት አመት 1ኛ አመት ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቶ ጌታቸው አበባየሁ የእቅድ፣ በጀት፣ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፋን ጨምሮ የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ እና የቢሮው የጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ኮራን ምላሽ ሰጥተዋል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.