
አንድ ሚሊየን ብር ሽልማት የሚያስገኘው
ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከሳኦል ኩነቶች አዘጋጅ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት በአይነቱ ልዩ የሆነው 2016 ኦፕን ቶርናመንት የቴኳንዶ ውድድር ነገ በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ፍጸሜውን እንደሚያገኝ ተገለጸ
በዝግጅቱ የፌድሬሽኑ ሥራ አስፈጻናሚ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አርቲስቶች፤ አምባሳደሮች ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች፣የስፖርት ባለሙያዎች እና አሰልጣኞች መታደማቸው ተመልክቷል።
በአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ኦፕን ቶርነመንት ውድድር ላይ ከተለያዩ ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ክፍለ ከተሞች ከ500 በላይ የሚሆኑ የቴኳንዶ ስፓርተኞች ለውድድር መቅረባቸውን የገለጹት የፌድሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ዋሲሁን እስከ ነገ ድረስ ያልመጡ የክልል ተወዳዳሪዎች የሚገኙ መሆኑን አሳውቀዋል።
ውድድሩ ግዙፍ እና በአይነቱ ልዩ ቢሆንም ፌድሬሽኑ ያሰበውን ማሳካት የቻለበት ነው ያሉት አቶ ጥላሁን የውድድሩ ሻምፒዮና ለሆኑ የቴኳንዶ ስፓርተኞች ከሜዳልያ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱን ገልጸዋል
የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ 2016/ 2024 ኦፕን ቶርናመንት ከግንቦት 3 እስከ 6 2016 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን የስፓርቱ አፍቃሪያንና መታደም የሚፈልጉ በሙሉ ጉለሌ መድኃኒያለም አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል እንዲመጡ ፌድሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.