ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት በቅንጅትና ትብብር በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት በቅንጅትና ትብብር በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ። ጥቅምት 25 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት በቅንጅትና ትብብር በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን የቢሮው ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በሩብ አመቱ በቅንጅትን እና ትብብር ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ገልፀው በቀጣይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል። የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሁሉም ተቋም በእቆዱ አካቶ ሊሰራው የሚገባው ተግባር ነው ያሉት አቶ ሚሊዮን የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የከተማ አስተዳደሩ ቁጥር አንድ አጀንዳ ነው ብለዋል። ቢሮው የከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ለማረጋገጥ ከ13 ተቋማት ጋር በቅንጅትና ትብብር እንደሚሰራ ፅ/ቤት ሀላፊው ተናግረዋል። በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ቢሮው በቅንጅትና ትብብር የሰራቸውን ስራዎች አቶ አብዱላሚድ ዴሌቦ የመልካም አስተዳደርና የለውጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ቢሮው በሩብ አመቱ በቅንጅትና ትብብር የሰራቸው ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ ወራትም የታቀዱ እቅዶችን ለማሳካት ከቢሮው በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.