በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ የመዝናኛ ስፍራዎች ወጣቶቾ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ እድል የሰጠ ነው። አቶ ዳዊት ትርፉ
በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ የመዝናኛ ስፍራዎች ወጣቶቾ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ እድል የሰጠ ነው። አቶ ዳዊት ትርፉ ጥቅምት 25 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ የመደመር መንግስት የወጣቶች የፖናል ውይይት በክፍለ ከተማው ጎሮ አከባቢ በኮሪደር ልማቱ በተሰራ የመዝናኛ ቦታ ላይ አካሄደ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና የስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ የመዝናኛ ቦታዎች ወጣቶች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲያደርጉ እድል የሰጠ ነው ብለዋል። ወጣቶች በሀገራቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ አንዳለባቸው የተናገሩት አቶ ዳዊት በዚህ ጊዜ በውይይት የሚያምን እና ምክንያታዊ የሆነ ወጣት መሆን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ወጣቶች ያሎቸውን ፀጋዎች፣ ክህሎቶች፣ እውቀቶች እና ልምዶች በመደመርና አብሮ ሰርቶ የማደግ ባህላቸውን በማጎልበት በሀገራቸው የብልፅግና ጉዞ አሻራቸውን ማስቀመጥ እንዳለባቸው ም/ቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዳ/ር አብይ አህመድ በተፃፈው የመደመር ትውልድ መፅሐፍ ዙሪያ ለፖናል ውይይት መነሻ ፁሁፍ አቅርበዋል። ወጣቶች አዳዲስ ፍልስፍናን፣ ፈጠራን እና የሀሳብ ሀይላቸውን በመደመር አገርን ለመለወጥ በሚያስችል መልኩ እንዲጠቀሙበት አቶ ክብረአለም ገልፀዋል። የመደመር ፅንሰ ሀሳብ በመንፈሳዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ እና በማህበራዊ ደረጃ ያለውን የአንድነት ሀሳብ አቶ ክብረአለም ባቀረቡት የመነሻ ፁሁፍ በዝርዝር ቀርቦል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አንዳለም ወጣቶች መንግስት የፈጠረላቸውን መልካም እድል የራሳቸውን ሂይወት በመቀየር መልኩ በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል። በፖናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች በበኩላቸው በኮሪደር ልማቱ የመዝናኛ ቦታዎችን ጨምሮ የተሰሩ የልማት ስራዎች ትርፍ ጊዚያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያሳልፉ እንዳረጋቸውና በማህበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ውይይት ለማድረግ እንደረዳቸው ገልፀዋል። በመደመር ፅንሰ ለችግሮቻቸው መፍትሔ ለስኬታቸው መዳረሻ መንገድ መግኝት እንደሚቻል በፖናል ውይይቱ መረዳት እንደቻሉ ወጣቶች ተናግረዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.