ቢሮው በክፍለ ከተሞች የሚያካሂደው የመደመር ትውልድ የወጣቶች የፖናል ውይይት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ጥቅምት 26 ቀን 2018ዓ.ም
ቢሮው በክፍለ ከተሞች የሚያካሂደው የመደመር ትውልድ የወጣቶች የፖናል ውይይት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ጥቅምት 26 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እያካሄደ የሚገኘው የመደመር መንግስት የወጣቶች የፖናል ውይይትን አጠናክሮ ቀጥሏል ዛሬ የመደመር መንግሥት መጽሐፍ መነሻ በማድረግ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተሰራ የኮሪደር ልማት በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ክብረአለም ደምሴ እና የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ም/ሀላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬን ጨምሮ የለሚ ኪራ ክፍለ ከተማ አመራሮችና የክፍለ ከተማው ወጣቶች በስፋት ተሳትፈውበታል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መደመር ላይ የጻፏቸው አራቱም መጽሐፍት ልማት እና ዘላቂ ብልጽግና ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውን ያስታወሱ አቶ ክብረአለም ደምሴ ወጣቶች የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ለአገር ዘላቂ ልማት፣ እና አንድነትና እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል ወጣቶች የንባብ ባህላቸውን በማዳበር የመደመር ፍልስፍናን የመረዳት እና ፍልስፍናውን ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ያወሱት አቶ ክብረአለም አገር በቀል ፍልስፍና መከተል ለአገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት መጽሐፍ አብሮነትና መተባበር ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ በሚሰጠው ጠቀሜታ ላይ ገለጻ ያደረገው የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ም/ሀላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬን የመደመር መንግሥት መጽሐፍ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በሌሎች ወሳኝ ዘርፎች ላይ ለሀገር በያዘው ቱርፋት ላይ ሰፊ ገለጻ አድርጓል የመደመር መንግሥት መፅሀፍ ታሪክን በአውዱ የመረዳት እና ኢትዮጵያ ጠንካራ አገረ መንግሥት እንዲኖራት መሰረት የሚጥል ነው ያሉት አቶ ዳዊት ፍልስፍናው ለአገር ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል። ወጣቶች የመደመርን ፅንሰ ሀሳብ አንበው ከመረዳት ባለፈ በተግባር በመኖር ከራሳቸው ህይወት ባለፈ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር ስራን ሰርተው ማለፍ እንዳለባቸው አቶ ዳዊት ተናግረዋል። በፖናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች በአሁኑ ጊዜ መንግስት ለወጣቶች በሰጠው ልዩ ትኩረት መደሰታቸውን ገልፀው እንደነዚህ አይነት ውይይቶች ወጣቱን ለስራ የሚያነሳሱ የሚያቀራርቡ እና በሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት ላይ ወሳኝ አካል መሆናቸውን ግንዛቤ የሚሰጡ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። የመደመር ትውልድ የወጣቶች የፖናል ውይይት በለሚ ኩራን ጨምሮ በቦሌ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በነገው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.