የመደመር ትውልድ የጀመረውን የሚጨርስ እና በአገር በቀል እሳቤ ልማትና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ነው። /አቶ ክብር ዓለም ደምሴ/
የመደመር ትውልድ የጀመረውን የሚጨርስ እና በአገር በቀል እሳቤ ልማትና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ነው። /አቶ ክብር ዓለም ደምሴ/ ጥቅምት 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የመደመር ትውልድ የጀመረውን የሚጨርስ እና በአገር በቀል እሳቤ ልማትና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር ዓለም ደምሴ ገለጹ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የመደመር መንግስት መጽሐፍ የወጣቶች የፖናል ውይይት ላይ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ክብር ዓለም ደምሴ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ኃላፊ አቶ ደረጀ ክንፈ፣የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ተክሌ እና ወጣቶች ተገኝተዋል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መደመር፣የመደመር መንገድ፣ የመደመር ትውልድ፣የመደመር መንግስት ጨምሮ ለሌሎች መጻሕፍት መጻፋቸው ያስታወሱት አቶ ክብር ዓለም ደምሴ አገራችን በፍጥነት ወደ ብልጽግናው ማማ እንድትወጣ መጽሐፉ በርካታ መንገዶችን እንደሚጠቁም ገልጸዋል ወግ አጥባቂው ትውልድ፣ሕልመኛው ትውልድ፣ውል አልባው ትውልድ፣ ባይተዋር ትውልድ እና የመደመር ትውልድ የሚሰኙ የኢትዮጵያን ትውልዶች ላይ ሰፊ ትንታኔ የሰጡት አቶ ክብርዓለም በመደመር እሳቤ ትውልዱ ሀገር ካለችበት ችግር እንድትወጣ አሻራውን እንዲያሳርፍ ለማመላከት የተፃፈ መጽሐፍ መሆኑን ገልጸዋል መደመር እልዩነቶችን በማስታረቅ፣ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊ አንድንትን ያጠናክራል ያሉት አቶ ደረጀ ክንፈ በአራቱም መጻሕፍት ውስጥ ጎልተው የሚታየው አገር የሚያሳድግ አገር በቀል ሐሳብ ነው ብለዋል የሽሮ ሜዳ አከባቢ ወጣቶችን የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራ ጥያቄ ለመለስ ከተማ አስተዳደሩ ለሰጠው ትኩረት ምስጋና ያቀረቡት የጉለሌ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ተክሌ መንግስት ለወጣቱ የሰጠው የላቀ ትኩረት በመደመር ውስጥ በስፋት እንደሚታይ ገልጸዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.