ለሰውነት ማጎልመሻ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም
ለሰውነት ማጎልመሻ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ለሰውነት ማጎልመሻ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ ከአስረ አንዱም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ ከ 450 በላይ የስፖርት መምህራን እየተሰጠ ያለው ስልጠና እስከ ጥር 30 2018 ዓ/ም እንደሚቆይ የገለጹት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ መምህራን ንጹሕ ስፓርትን ለማስፈን እና ትውልድ ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የመምህራን የስልጠና ፍላጎት መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጎሳዬ ለተከታታይ አራት ወራት ቅዳሜ እና እሁድ በሚሰጠው ስልጠና የልዩ ልዩ ስፖርት አይነቶች የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ የሰልጠናው የዛሬ ቆይታ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዶፒንግ ምንነት፣የህግ ጥሰቶች፣የስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ የተደረገ ሰሆን የተከለከለ አበረታች ቅመም መጠቀም ያልተገባ ውጤት ለማስመዝገብ መጣር ወንጀል ከመሆኑ ባሻገር በአገር ገጽታ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው አመላክተዋል የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞችን መጠቀም በጤናቸው የሚያስከትለውን አዕምሮዊና አካላዊ የጎንዮሽ ጉዳት እንዲረዱ የስፖርት መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ማስቻል መሆኑን ያወሱት አሰልጣኞቹ ከዶፒንግ ነፃ የሆነ ስፖርትና ስፖርተኞችን ለማፍራት ትምህርት ቤቶች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ ስፖርት መምህራን የሚሰጠው ስልጠና በእግር ኳስ፣ በቮሊ ቦል፣ በአትሌቲክስ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.