የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር የአርቲፊሻል ኢን...

image description
- ውስጥ supporter    0

የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትኩረት በማድረግ ተካሄደ

የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትኩረት በማድረግ ተካሄደ

ሕዳር 1 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ዘውትር ሰኞ የሚያካሂደው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መድረክ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ላይ ትኩረት በማድግ ተካሄደ

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስን በመጠቀም የአገልግሎት ዘርፋውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ጠቅሰው ሰው ሰራሽ ልሕቀት ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ልማትን ብልጽግናን ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል፡፡

በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ ቆየው ስልጠናን ለሰራተኛው እና ለወጣቱ ለማድረስ እንደሚሰራ ያወሱት አቶ በላይ በመደመር ትውልድ ወደ ብልፅግና የሚደረገው ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ሰራተኛ ኃላፊነጹን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዛሬውን የዕውቀት ሽግግር መድረክ ላይ ያላቸውን ዕውቀት ያጋሩት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር ዓለም ደምሴ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር 1950 ጀምሮ ኤአይ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን አስተዋሰው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጽንሰ-ሐሳብን ከቴክኒካዊ ገደቦች እና ስላለው ጠቀሜታ እና ስጋቶች ዝርዝር ማብራያ ሰጥተዋል፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በውስጡ ሦስት መሠረታዊ የሆኑ ሱፐርቫይዘር፣አንሱፐርቫይዘር እና ሪፎርስመንት የሚባሉ የአስተምሮ ጭብጦች እንዳሉት ያወሱት አቶ ክብርዓለም ሰራተኛው ቴክኖሎጂን መቀበል መጠቀም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተገቢው መልኩ በመማር ስራቸውን ማቀላጠፍ እንዳባቸው አሳስበዋል፡፡

የዕውቀት ሽግግር መድረኮች አብሮነት የሚያጠናክሩ፣አቅም መገንቢያ እና ልምድ የምንለዋወጥባቸው መድረኮች ናቸው ያሉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ ውስጣዊ አሰራር የሚያጠናክሩ ርዕሰ ጉዳዮቸ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚያተኩረውን ልምድ ያካፈሉት የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ ራስን በማብቀት የምንሰጠውን አገልግሎት በሥነ ምግባር እና ስራን አውቆ በመስራት እንደሚተገበር አመላክተዋል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.